“ በ ወለጋ ጃርደጋ ጃርቴ ወረዳ የ ነቀተኒ የጋብቻ ስነስርአት ከትዉፊታዊ ተዉኔት አላባዉያን አንፃር”
Files
Date
2022-06
Authors
Journal Title
Journal ISSN
Volume Title
Publisher
Wolkite University
Abstract
ይህ ጥናታዊ ፅሁፍ በዋናነት የሚያተኩረው በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ሆሮ ጉድሩ ዞን በጃር
ደጋ ጃርቴ ወረዳ የነቀተኒ የጋብቻ ስነስርዓት ከትውፊታዊ ተውኔት አላባውያን አንፃር እና የነቀተኒ
ክንዋኔዎችን በማዋሀድ ትውፊታዊ ይዘቱን እና ከተውኔት አላባውያን ጋር ያለውን ጥምረት
መተንተን ነው። አጥኚ ለጥናቱ ገላጭ የምርምር ዘዴን ይጠቀማል ። የነቀተኒ የጋብቻ ስነስርአት
በሚከወንበት ሂደት ውስጥ የቃላት ምልልስ (ቃለ ተውኔት) ፣ አልባሳት ፣ ምርቃት ፣ ቁሳቁስ
፣ የመከወኛ ቦታ (መቼት) ፣ ዘፈን ፣ ውዝዋዜ ፣ በአጠቃላይ ስለ ባህሉ ከትውፊታዊ ተውኔት
ጋር በማጣመር ስለ ትውፊታዊ ተውኔት የተፃፉ መፅሀፍትን እና ተዛማጅ ፅሁፎችን በመዳሰስ
እንዲሁም ምልከታ እና መዛግብትን የመረጃ መሰብሰቢያ ዘዴ አድርጎ በመጠቀም ይህ ጥናት
ትንታኔ ሰጥቷል ።