በሬሳ መርጋ, በሬሳ2024-02-212024-02-212022-06http://10.194.1.109:8080/xmlui/handle/123456789/370ይህ ጥናታዊ ፅሁፍ በዋናነት የሚያተኩረው በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ሆሮ ጉድሩ ዞን በጃር ደጋ ጃርቴ ወረዳ የነቀተኒ የጋብቻ ስነስርዓት ከትውፊታዊ ተውኔት አላባውያን አንፃር እና የነቀተኒ ክንዋኔዎችን በማዋሀድ ትውፊታዊ ይዘቱን እና ከተውኔት አላባውያን ጋር ያለውን ጥምረት መተንተን ነው። አጥኚ ለጥናቱ ገላጭ የምርምር ዘዴን ይጠቀማል ። የነቀተኒ የጋብቻ ስነስርአት በሚከወንበት ሂደት ውስጥ የቃላት ምልልስ (ቃለ ተውኔት) ፣ አልባሳት ፣ ምርቃት ፣ ቁሳቁስ ፣ የመከወኛ ቦታ (መቼት) ፣ ዘፈን ፣ ውዝዋዜ ፣ በአጠቃላይ ስለ ባህሉ ከትውፊታዊ ተውኔት ጋር በማጣመር ስለ ትውፊታዊ ተውኔት የተፃፉ መፅሀፍትን እና ተዛማጅ ፅሁፎችን በመዳሰስ እንዲሁም ምልከታ እና መዛግብትን የመረጃ መሰብሰቢያ ዘዴ አድርጎ በመጠቀም ይህ ጥናት ትንታኔ ሰጥቷል ።en“ በ ወለጋ ጃርደጋ ጃርቴ ወረዳ የ ነቀተኒ የጋብቻ ስነስርአት ከትዉፊታዊ ተዉኔት አላባዉያን አንፃር”Thesis