ወልቂጤ ዩንቨርስቲ የማህበረሰብ እና ስነ ሰብ ኮሌጅ የቴአትር ጥበባት ትምህርት ክፍል ፀዳል ዉስን ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ ከገፀ-ባህርያት አሳሳል አንፃር ትንተና በ ሱራፌል አይጎታ ወልቂጤ ዩንቨርስቲ ሚያዚያ/2017 ዓ.ም ፀዳል ዉስን ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ ከገፀ-ባህርያት አሳሳል አንፃር ትንተና በ ሱራፌል አይጎታ ፧ የጥናቱ አማካሪ መምህርት ሜሮን ተስፋዬ በማህበራዊ ሳይንስ እና ስነ ሰብ ኮሌጅ ለቴአትር ጥበባት ትምህርት ክፍል ለአርትስ ባችለር ዲግሪ ማሟያ የቀረበ ጥናታዊ ፅሁፍ የአማካሪው ማረጋገጫ ይህ ጥናታዊ ፅሁፍ በወልቂጤ ዩኒቨርስቲ የቴአትር ጥበባት ትምህርት ክፍል የመጀመሪያ ድግሪ ማሟያ መስፈርት መሰረት ድጋፍ የተደረገለት መሆኑን አረጋግጣለሁ። የአማካሪው ስም____________________________ ፊርማ__________________________________ ቀን____________________________________ ይህ ጥናት በ ሱራፌል አይጎታ ፀዳል ዉስን ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ ከገፀ-ባህርያት አንፃር ትንተና በሚል ርዕስ የሰራዉን የመጀመሪያ ድግሪ ሟሟያ ፅሁፍ የዩኒቨርስቲውን ጥራት እና ደረጃ ያሟላ ለቴአትር ጥበባት ትምህርት ክፍል ተቀባይነት መሆኑን ማረጋገጫ ነው። ይህም በፈታኝ ኮሚቴ ተረጋግጧል። ፈታኝ አንድ ስም___________________________ ፊርማ________________________ ቀን__________________________ ፈታኝ ሁለት ስም____________________________ ፊርማ__________________________ ቀን___________________________ I ምስጋና በመጀመርያ ለዝህ ቀን ላደረሰኝ መጠግያ፣ረዳቴ እና ተስፋዬ ለሆነኝ ለልኡል እግዚአብሄር ምስጋና ይሁንለት በመቀጠል ከፈጣሪ በታችሙሉ ህይወታቸውን ገብረው እዚህ እንድደርስ ብዙ ዋጋ ለከፈሉልኝ ለአባቴ አይጎታ አንሳ እና ለውድ እናቴ አቤቤች አጀባ እንዲሁም ለ ሰለሞን አንኩቴ ይህንን ጥናታዊ ፅሁፍ በምሰራበት ወቅት በትዕግስት እና በትጋት በፍፁም ትህትና ስህተቴን በማረም በማስተካከል ከፍተኛ ድጋፍ ላደረገችልኝ አማካሪዬ መምህርት ሜሮን ቴስፋዬ ምስጋናዬ እጅግ ከፍ ያለ ነው ። በተጨማሪም ይህንን ጥናታዊ ጽሁፊ ስሰራ ከጎኔ ለነበረ ለ ሀይለየሱስ ሰዉነት እና ለግቢ ጓደኞቼ እንድሁም ለዉዱ የትምህርት ክፍል ጓደኞቼ ፈጣሪ ዕድሜ እናጤና ይስጣችሁ ። II አበርክቶ በሁሉም ነገር ለምረዱኝ ወልደዉ አሳድገዉኝ እስከ ዛረዋ ቀን ድረስ ከጎነ ለነበሩ፤የራሳቸዉን ፍላጎት ሳያሳኩ ለኔ በመጨነቅና በማሰብ ላስተማሩኝ ለውድ ቤተሰቦቸ ይሁንልኝ። III አጠቃሎ ይህ ጥናታዊ ጽሁፊ ፀዳል ዉስን ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ ከ ገፀ-ባህርያት አንፃር ተንትኖ የምያቀርብ ነዉ።ጥናቱ የተሰራበት ዘዴም ገላጭ ስሆን የተጠቀመዉ የመረጃ አሰባሰብ ዘዴ ፊልሙን በመመልከትና ተያያዥነት ያላቸዉን ፅሁፎች በማንበብ ነዉ።ጥናቱ በዋናነት የሚያጠነጥነው ፀዳል በተባለች ሴት ገፀባህርይ የትዳር ህይወት ላይ በሚገጥማት ውስጣዊና ውጫዊ ከራሷ ጋር ከሰዎች ጋር በምታደርገው ግጭት ላይ ስሆን ጥናቱ መሰረት የምያረገዉም አካላዊ የገፀባህሪያት አሳሳል፣ማህበራዊ የገፀባህሪያት አሳሳል፣ስነልቦናዊ የገፀባህሪያት አሳሳል እና ግብረገባዊ የገፀባህሪያት አሳሳል ላይ ነዉ።ጥናቱ የምያነሳቸዉ ሀሳቦችም የገፀ- ባህርያትን ድክመት እና ጥንካሬ በማሳየት የራሱን አስተዋጽኦ ያደርጋል።በመጨረሻም ማጠቃለያ እና የመፍትሔ ሀሳቦች በመግለፅ ጥናታዊ ጽሁፉን አጠናቋል ። ማውጫ ገጽ ምስጋና ........................................................................I አበርክቶ ...................................................................... II አጠቃሎ ..................................................................... III ምዕራፍ አንድ .................................................................... 1 1. መግቢያ .....................................................................1 1.1 የጥናቱ ዳራ ..............................................................2 1.2 የጥናቱ አላማ ............................................................ 2 1.2.1 የጥናቱ አብይ አላማ ................................................... 2 1.2.2 የጥናቱ ውስን አላማ ...................................................2 1.3 የጥናቱ ጠቀሜታ ...........................................................2 1.4 ጥናቱ የሚያነሳቸው ጥያቄዎች ...................................................3 1.5 የጥናቱ ዘዴ .............................................................. 3 1.6 የጥናቱ ወሰን .............................................................3 1.7 የጥናቱ አደረጃጀት .......................................................... 3 ምዕራፍ ሁለት ....................................................................5 2.ክለሳ ድርሳናት ................................................................. 5 2.1 የፊልም ምንነት ........................................................... 5 2.2 የፊልም ፅሁፍ አላባውያን ......................................................5 2.3 የገፀባህሪያት ምንነት ........................................................ 6 2.4.ገፀባሕርያት የሚሳሉበት መንገዶች ................................................6 2.4.1 አካላዊ የገፀባህሪያት አሳሳል .............................................. 7 2.4.2 ማህበራዊ የገፀባህሪያት አሳሳል ............................................ 7 2.4.3 ስነልቦናዊ የገፀባህሪያት አሳሳል .............................................8 2.4.4 ግብረ-ገባዊ የገፀባህሪያት አሳሳል ........................................... 8 2.5 የተዛማጅ ፅሁፍ ቅኝት ....................................................... 8 ምዕራፍ ሶስት ...................................................................10 3. የመረጃ ትንተና ............................................................... 10 3.1 የፀዳል ውስን ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ ታሪክ ...................................... 10 3.2 የፀዳል ውስን ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ ገፀባሕርያት አሳሳል .............................. 11 3.2.1 ፀዳል ........................................................... 11 ሀ. የፀዳል አካላዊ አሳሳል .............................................11 ለ. የፀዳል ማህበራዊ አሳሳል ........................................... 11 ሐ.የፀዳል ስነ-ልቦናዊ አሳሳል .......................................... 12 ሐ. የፀዳል ግብረ-ገባዊ አሳሳል ......................................... 12 3.2.2 ዳግም ...........................................................13 ሀ. የዳግም አካላዊ አሳሳል ............................................ 13 ለ. የዳግም ማህበራዊ አሳሳል .......................................... 13 ሐ. የዳግም ስነልቦናዊ አሳሳል .......................................... 13 መ. ግብረ-ገባዊ አሳሳል ............................................. 14 3.2.3 ናሆም .......................................................... 14 ሀ. የናሆም አካላዊ አሳሳል ............................................ 14 ለ. የናሆም ማህበራዊ አሳሳል .......................................... 14 ሐ. የናሆም ስነልቦናዊ አሳሳል .......................................... 14 መ. የናሆም ግብረ-ገባዊ አሳሳል ........................................ 15 3.2.4 የዳግም እናት ...................................................... 15 ሀ. የዳግም እናት አካላዊ አሳሳል ........................................ 15 ለ. የዳግም እናት ማህበራዊ አሳሳል ....................................... 15 ሐ. የዳግም እናት ስነልቦናዊ አሳሳል .......................................15 መ. የዳግም እናት ግብረገባዊ አሳሳል ...................................... 16 3.2.5 ሶፊ ............................................................ 16 ሀ. የሶፊ አካላዊ አሳሳል ..............................................16 ለ. የሶፊ ማህበራዊ አሳሳል ............................................ 16 ሐ. የሶፊ ስነልቦናዊ አሳሳል ............................................16 መ. የሶፊ ግብረገባዊ አሳሳል ........................................... 17 ምዕራፍ አራት ...................................................................18 4 ማጠቃለያ ....................................................................18 4.1 የመፊትሄ ሀሳብ .......................................................... 19 ዋቢ መጽሀፋት .................................................................. 20 1 ምዕራፍ አንድ 1. መግቢያ ጥበብ በዚህ አለም ለብዙ ዘመናት የኖረ ከሰው ልጅ የዕለት ከዕለት ኑሮ ጋር እየዳበረ እና እያደገ የመጣ የሰውን ልጅ አኗኗር የኢኮኖሚ ደረጃ እንዲሁም ገጠመኞችን በማዋሃድ ነሚያስተምር እና የሚያዝናና አንዱ የሰው ልጅ ልዩ ችሎታ ነው። ፊልም ከኪነጥበብ ስራዎች አንዱ ሲሆን በተደጋጋሚ የሚንቀሳቀሱ ምስሎች እና ድምፅን በመጠቀም ታሪኮችን የምናስተላልፍበት መንገድ ነው። ፊልም ከሌሎች የኪነጥበብ ስራዎች ውስጥ ይበልጥ እንዲወደድ እና ትኩረት እንዲሰጠው የሚያደርገው ምስልንና ድምፅን በመጠቀም ታሪክን ስለሚያስተላልፍ ነው። ይህ አይነቱ ታሪክን የመንገሪያ ጥበብ ዛሬ የደረሰበት ደረጃ ለመድረስ ከመቶ ሰላሳ አመት በላይ ታሪካዊ የለውጥ ሂደቶችን አሳልፏል። በዚህም ታሪክ ከድምፅ አልባ ፊልም ጀምሮ አሁን ያለበት ደረጃ ለመድረስ ብዙ ለውጦችን አሳልፏል። በድምፅ አልባ የፊልም ጥበብ ውስጥ ስማቸው በትልኩ ከሚጠሩት ሰዎች መካከል ቻርሊ ቻፕሊ ዋናው ነው። የጀርመኑ ቢል ዳግለስ ሲኒማ ሙዚየም (https://www.bdcmuseum.org.uk) እንዲህ ሲሉ ስለ ፊልም አመጣጥ በገፃቸው አስቀምጠዋል። " በ1929 ገደማ ድምፅ በመቅረጫ በመፈጠሩ ምስልንና ድምፅን በመጠቀም የተለያዩ ሀሳቦችንና ትምህርቶችን የምንፈጥርበትና የምናቀርብበት አንዱ መንገድ ሁኗል" ከዚህም በመነሳት ፊልም ከብዙ የለውጥ ሂደቶች በኋላ አሁን ያለበት ደረጃ ለመድረስ ችሏል። እንዲሁም https://www.bamlakuasmare.blogsport.com እንዲህ ሲሉ ስለ ድራማ በገፃቸው አስቀምጠዋል።ድራማ የሚለዉ ቃል የእንግሊዘኛ ቃል ሲሆን ተዉኔት የሚለዉን የአማርኛ ቃል እንዲወክል ተደርጎ የተሰየመ ቃል ነዉ። ተዉኔት በግጥም ወይም በተዋንያን ድርጊትና ምልልስ ታጅቦ በመድረክ ላይ የሚተወን ድርሰት ነዉ። አንዳንድ ሰዎች ድራማን ትያትር፣ ቤተ ተዉኔት፣ መራሂ ተዉኔት እያሉ ሲጠሩት ይስተዋላል። ነገር ግን እነዚህ ከድራማ ጋር ግንኙነት ያላቸዉ እንጂ ድራማን የሚወክሉ አይደሉም።ድራማ መቼ እና የት ተጀመረ ለሚለዉ ጥያቄ ቁርጥ ያለ መልስ ማግኘት አይቻልም። ምክናያቱም የድራማ ቀለምና አሻራ ያላቸዉ የሥነ ጽሑፍ ዘርፎች በርካታ ከመሆናቸዉ የተነሳ ነዉ። ነገር ግን መደበኛ መልክ አስይዞ ድራማን ለተደራስያን በማቅረብ ረገድ ግሪኮችን ቀድሞ የተገኘ የለም። በዚች ሀገር ድራማ ከ2200 ዘመናት በፊት ከጥንታዊዉ የግሪክ ንጉስ ከዳዮናይሲስ ጋር ተያይዞ የተፈጠረ ነዉ። 2 1.1 የጥናቱ ዳራ በሀገራችን ኢትዮጵያዊ በአሁኑ ሰዓት ረጅም ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ እና ውስን ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ ከአለፉት አመታት ጋር ስናነፃፅረው ጥሩ የሚባል መነቃቃትን እያሳየ ይገኛል። ከእነዚህም ፊልሞች መካከል ፀዳል ውስን ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ አንዱ ነው። ፀዳል ውስን ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ ደራሲዋ ትዕግሥት መዝገቡ፤ አዘጋጆቹ ፀዳል ፋንታሁን እና ሰውመሆን ፊልም ፕሮዳክሽን በ2016 ዓ.ም ለተመልካች የቀረበ ፊልም ነው። አጥኝውም ይህንን ጥናታዊ ፅሁፍ ለመስራት ያነሳሳው ፀዳል ውስን ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ ከገፀባህሪያት አሳሳል ለመተንተን ፍላጎት ስላደረበት ነው። 1.2 የጥናቱ አላማ 1.2.1 የጥናቱ አብይ አላማ የዚህ ጥናታዊ ፅሁፍ አብይ አላማው ፀዳል ውስን ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ ከገፀባህሪያት አሳሳል አንፃር መተንተን ነው። 1.2.2 የጥናቱ ውስን አላማ  ፀዳል ውስን ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ በተሰኘዉ ፊልም ያሉትን ገፀባሕርያት ከገፀባሕርያት አንፃር መተንተን እና ማሳወቅ ነው ።  በፀዳል ውስን ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ ላይ ያሉትን ድክመቶች በመለየት ወደፊት ጥሩ ዉስን ተከታታይ ድራማዎች እንድሰራ ይረዳል ። 1.3 የጥናቱ ጠቀሜታ  በፀዳል ውስን ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ ላይ ያሉትን ድክመቶች በመለየት ወደፊት ጥሩ ውስን ተከታታይ ድራማዎች እንዲሰሩ ይረዳል።  ገፀባሕርያት እንዴት መገንባት እና መሰራት እንዳለባቸው ያሳውቃል።  በድርሰትና በዝግጅት ላይ ያሉ ባለሙያዎች የተሻለ ገፀባህሪ በተመለከት ስራ እንዲሰሩና ስህተት ካለባቸው እንዲያስተካክሉ ሌሎች ስራዎቻቸውን እንዲገመግሙ መንገድ ይከፍታል።  ለሌሎች አጥኝዎች እንደ ግብዐት ያገለግላል። 3 1.4 ጥናቱ የሚያነሳቸው ጥያቄዎች  ፊልም ምንድን ነው?  የገፀባህሪ አሳሳል ባህሪያት ምንድን ናቸው?  ፀዳል ውስን ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ ከገፀባህሪያት አሳሳል አንፃር ምን ይመስላል?  የፀዳል ውስን ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ ገፀባሕርያት አሳሳል ደካማና ጠንካራ ጎን ምን ይመስላል? 1.5 የጥናቱ ዘዴ ያለው እንዳወቀ " የምርምር መሰረታዊ መርሆች አተገባበር"(2009፥21) በሚለው መፅሀፉ ውስጥ ስለ ገላጭ የምርምር ዘዴ እንዲህ ሲል ይገልፃል። " ገላጭ ምርምር ስሙ እንደሚያመለክተው ተመራማሪው አንድን ጉዳይ አንስቶ ችግሩ ምን ያህል አሳሳቢ እንደሆነ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ መሰረት አድርጎ በትረካ መንገድ የሚቀርብበት ነው" በማለት ገልጿል።ይህ ጥናታዊ ፅሁፍ ገላጭ የሚባለውን የምርምር ዘዴ ሲሆን የሚጠቀመው አጥኝው በዚህ የምርምር ዘዴ መረጃን የሚሰበስብበት መንገዶች፦ ፨ ፀዳል ውስን ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማን በተደጋጋሚ በመመልከት ፨ መፅሀፍትን በማንበብ ፨ በገፀባህርያት አሳሳል ዙሪያ የተሰሩ ጥናታዊ ፅሁፎችን በማንበብ ነው። አጥኝው ይሄንን መንገድ በመጠቀም ፀዳል ውስን ተከታታይ ድራማ የሚተነትን ይሆናል። 1.6 የጥናቱ ወሰን ይህ ጥናታዊ ፅሁፍ ፀዳል ውስን ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማን ከገፀባህሪያት አሳሳል አንፃር ምን ይመስላል የሚለውን ብቻ መተንተን ብቻ ነው። 1.7 የጥናቱ አደረጃጀት የዚህ ጥናታዊ ፅሁም አደረጃጀት በአራት ምዕራፎች የተዋቀረ ነው። በምዕራፍ አንድ ምስጋና፤ አጠቃሎ፤ መግቢያ፤ የጥናቱ ዳራ፤ የጥናቱ አላማ፤ የጥናቱ አብይ አላማ፤ የጥናቱ ንዑስ አላማ፤ የጥናቱ ጠቀሜታ፤ ጥናቱ የሚያነሳቸው ጥያቄዎች፤ የጥናቱ ዘ፤ የጥናቱ ወሰን፤ የጥናቱ ወሰን እና በጥናቱ ወቅት ያጋጠሙ ችግሮች ናቸው። በምዕራፍ ሁለት ክለሳ ድርሳናት፤ የፊልም ምንነት፤ የገፀባህሪያት ምንነት፤ 4 የገፀባህሪያት አሳሳል ደረጃ፤ ስነልቦናዊ የገፀባህሪያት አሳሳል ደረጃ፤ ሞራላዊ የገፀባህሪያት አሳሳል ደረጃ እና የተዛማጅ ፅሁፍ ቅኝት ናቸው። በምዕራፍ ሶስት ደግሞ የመረጃ ትንተና፤ ፀዳል ውስን ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ ታሪክ፤ ፀዳል ውስን ተከታታይ ድራማ ከገፀባህሪያት አሳሳል አንፃር ናቸው። ምዕራፍ አራት ደግሞ ማጠቃለያ፤ የመፍትሄ ሀሳብና ዋቢ መፅሀፍትን አጠቃሎ ይዟል። 5 ምዕራፍ ሁለት 2.ክለሳ ድርሳናት 2.1 የፊልም ምንነት የፊልም የሚታይ የምስል ጥበብ ነው። ፊልም የሰውን ልጅ ህይወት ከውልደት እስከ ሞቱ ባለበት ጊዜ ውስጥ የሚያገኘውን ማንኛንም ነገር መልካም ሆነ መጥፎ ደስታ ሆነ ሀዘን ማግኘት ማጣቱን ምኞት ተስፋውን እዚህ አለም ላይ የሚፈጠሩ ነጠሮችን ድርሰት በምንለው የስነፅሁፍ ዘርፍ ተደርሶ ታሪክን ከመንገር ባለፈ በማሳየት ለተመልካቾች የሚቀርብ የጥበብ ሙያ ነው። ይህን ሀሳብ አዲስ ተስፋ" የፊልም አፃፃፍ ብልሀት"በተሰኘው መፅሀፉ እንዲህ ሲል ገልጿል፦ ፊልም ታሪክን በምስል (ድርጊትና እንቅስቃሴ ቅንብር) የመግለፅ እና የመንገር ጥበብ ነው። ፊልም ታሪኩን የሚሸከሙ ባለታሪኮች የጊዜ የቦታ ገደብ ሳይኖርባቸው የሚያስቡትን፤ የሚኖሩትን፤ የሚገጥማቸውን ችግርና የሚወጡበትን ስልት ለተመልካች በማውራት ብቻ ሳይሆን በማሳየት የመንገሪያ መንገድ ነው። ፊልም ከመናገር ይልቅ ታሪክን በማሳየት የመንገሪያ ጥበብ ነው። ይህ ሲባል ግን ንግግር የለም ወይም አያስፈልግም ማለት እንዳልሆነ ልብ ሊባል ይገባል። (2005፥24) ከዚህ ጋር ተያያዥነት ያለው ዘላለም ተፈራ " የፊልም ትወና ጥበብ" በተሰኘው መፅሀፍ ስለ ፊልም ምንነት እንዲህ ሲል ገልጿል። "የፊልም ጥበብ በተንቀሳቃሽ ምስሎች አማካኝነት ለተደራሲያን ታሪክ የምንናገርበት፤ ማህበራዊ አኗኗር፤ የኢኮኖሚ ደረጃ ወቅታዊ ጉዳዮች እና ታሪካዊ ክስተቶች ለተመልካች የሚታይበት ልዩ ልዩ ጥበብ ነው። የፊልም ምንነትን የበለጠ ለመረዳት ከሌሎች የጥበብ ዘርፎች ጋር ያለውን ልዩነት ማየት ተገቢ ነው።" (2010፥31) ስለዚህ ፊልም ከምንሰማው ይልቅ በአይናችን ተመልክተን የምንረዳው በታሪኩ ውስጥ ገብተን እራሳችንን የታሪኩ አካል አድርገን የምንመለከትበት አንዱ የጥበብ ሙያ ነው። 2.2 የፊልም ፅሁፍ አላባውያን ስለ ፊልም ፅሁፍ ሲነሳ ቀዳሚውን ቦታ የሚይዘው አላባዊያኖች ናቸው። የፊልም አላባውያን በፊልም ፅሁፍ ውሰጥ እንደ ጀርባ አጥንት የሚያገለግሉ ሲሆኑ አንድ የፊልም ታሪክ ቅርፁን ይዞና አምሮ እንዲሰራ መሰረት የሚሆኑት አላባዊያን ናቸው። እነሱም ታሪክ፤ ገፀባህርይ፤ ሴራ ግጭት፤ መቼት እና ቃለ ተውኔት ናቸው። ይህን ሀሳብ በአዲስ ተስፋ መፅሀፍ እንዲህ ተገልፃል፦ "ፊልም በድራማ መዋቅራዊ አውድ 6 አማካይነት በምስልና ቃለ ተውኔት ታሪክን የመግለፅ ጥበብ ነው። ታሪክን በምስልና በፎቶ የመግለፅ ጥበብን ተጠቅሞ ለማቅረብ የሚረዱ የፊልም መዋቅር መገንቢያ አካላትም አላባዊያን ብለን አንጠራቸዋለን እነዚህም ታሪክ፤ ገፀባህርይ፤ ሴራ፤ ግጭት፤ መቼትና ቃለ ተውኔት ሆነው እናገኛቸዋለን"(2005፥71) ከእነዚህም ከተዘረዘሩት አላባዊያን ውስጥ አጥኝው ጥናቱን የሚሰራው በገፀባህሪያት ላይ እንደመሆኑ መጠን አሳሳላቸው ላይ የሚያተኩር ይሆናል። 2.3 የገፀባህሪያት ምንነት ስለ ገፀባሕርያት አዲስ ተስፋ በመፅሀፉ እንዲህ ሲል ገልጿል፦ ገፀባህርያት ማለት ደራሲው ሊተርክ ያሰበውን ታሪክ የሚሸከም ሰው፤ እንስሳት ወይም ሰውኛ ሰብእና የሚላበስ ማንኛውም ነገር ይወክላል። የሰውን ባህርይ የሚወክል እንደሰው የሚወድቅና የሚነሳ ነው። ፀሀፊው በጥናቱ ያዳበረውን ሀሳቡን ለመናገር የሚረዳው ታሪኩን የሚሸከምለት የታሪኩ ባለቤት ያስፈልገዋል። ምክንያቱም በየትኛውም የድራማ ፅሁፍ ውስጥ በፅሁፍ ደረጃ በመጀመሪያ ፀሀፊው ሊመልሰው የሚገባው ጥያቄ "ይሄ ታሪክ የማን ነው" የሚለው ነው። አንድ ፀሀፊ ይዞት የተነሳውን ሀሳብ በተፈለገውና በተመረጠው ሰአት መጥኖ ለማሳየት የሚፈጥረው ገፀባህርይ ሙሉና የታሪኩ ባለቤት ሆኖ ተመልካቹ እያንዳንዱን የታሪኩን ውጣ ውረድ እየተከተሉ ያየው ዘንድ አሳማኝ በሆነ መንገድ መቀረፅ አለበት" (2005፥72) ገፀባሕርያት አንድ ደራሲ ሀሳቡን ለመግለፅ ታሪኩን ለማስጀመርም ለማስጨረስም የሚፈጥራቸው አካላት ናቸው። ገፀባሕርያት በጣም ጠቃሚ ከሚባሉ የፊልም አላባዊያን ውስጥ አንዱ ሲሆን የታሪኩ ባለቤት ወይም የታሪኩ ተሳታፊ በመባል የሚታወቁ ናቸው። ገፀባሕርያት ሲባሉ በታሪኩ ውስጥ ተስለው የሚገኙ ሰዎች፤ እንስሳት፤ ግዑዝ ነገሮች እንዱሁም መንፈሶችን የሚወክሉ አካላቶች ናቸው። 2.4.ገፀባሕርያት የሚሳሉበት መንገዶች ገፀባሕርያት የሚሳሉበት መንገድ በአራት የተከፋፈሉ እና የሰውን ልጅ የእለት ከእለት አንቅስቃሴ ያማከሉ ተደርገው የተዋቀሩ ናቸው ይህንን ሀሳብ ፈንታሁን እንግዳ "የተውኔት አፃፃፍ ዘዴ" በሚለው መፅሀፉ አንዲህ ያብራራል፦ ገፀ-ባህሪ የሚለው ቃል በፈጠራ ታሪክ ውስጥ ያሉትን የድርሰቱን ሰዎች (አበበ፣ ከበደ፣ አልማዝ)፣ በድርስቱ ውስጥ የተሳሉትን እንሰሳት (አህያ፣ ጅብ፣ በግ፣ ቀበሮ)፣ በተውኔታዊ ታሪኩ ውስጥ የሚቀረፁትን ሰማያዊ ወይም ሃተታ ተፈጥሯዊ ፍጥረታትና መናፍስት (ሰይጣናት፣ መላእክት! ሠናይመናፍስት፣ አኩይ መናፍ ስት፣ ጣዕረ-መንፈስ) እና እረቂቅ ሃሳቦችን (ተንኮል፣ ደግነት፣ መልካም ሥራ፣ ቁንጅና) የመሳሰሉትን ይወክላል። በሌላ በኩል 7 ደግሞ በፈ ጠራ ሥራ ውስጥ የሚገኙትን የድርሰቱን ሰዎች የሞራል፣ የሥነ-ምግባር፣ የሥነ- ልቦና በአጠቃላይየውስጣዊ ፀባይንና የውጫዊ አመልን ድምር መልክ የሚወክል ትርጓሜንም ይሸከማል:: ጠቅለል ባለመልኩ ሲገለፅ ገፁ ባህሪ የሚለው ቃል የድርስቱን ባለታሪክ አካላዊ ገፅታ፣ ውስጣዊ ፀባይና አስተሳሰብ በአንድነት የሚሸከም ነው፡፡ (2009፥ 25) 2.4.1 አካላዊ የገፀባህሪያት አሳሳል አካላዊ የገፀባህሪት አሳሳል ደረጃ እንዲሁ በእይታ ብቻ ልንገልፃቸው የምንችልና የምንስላቸው የአሳሳል አይነት ነው። ፈንታሁን እንግዳ በመፅሀፉ እንዲህ ገልፆታል፦ ከምንም በፊት ምንነታቸው ለአንባቢም ሆነ ለተመልካች ይፋ የሚሆነው በመጀመሪያ የገፀባህሪያት አሳሳል ደረጃ ማለት በነፍስ ወከፍ አቋማቸው ገለፃ አማካኝነት ነው። እንቅስቃሴ፤ ጤና፤ ድምፅ፤ መልክ፤ ጥቁረት፤ ንጣት ጠይምነት፤ አቋምን ማለትም ውፍረት፤ ቅጥነት፤ ርዝመት፤ እጥረት ምን እንደሆነ ያስረዳል። ይህ የአሳሳል ደረጃ አይነት ከስሙ እንደሚነሳው የእያንዳንዱ ገፀባህራዚያት ውጫዊ ክፍል ላይ ያተኮረ ሲሆን ይህን የአሳሳል አይነት አይተን ልንናገረው የምንችልበት ክፍል ነው። የገፀባህሪያት አካላዊ ቀረፃ ብዙ ጥበብን የሚጠይቅ አይደለም። ልክ በመንገድ ከሚያልፉ ሰዎች የአንዱን አቋም ተመልከተን ከምንናገረው የተለየ አይደለም። መዚህ ምክንያት ታዲያ የገፀባህሪያት የመጀመሪያ ደረጃ አሳሳል ማለትም የአካላዊ አቋማቸው ቀረፃ በጣም ቀላሉ የገፀባህሪያት አሳሳል ተደርጎ ይወሰዳል።(2009፥27) 2.4.2 ማህበራዊ የገፀባህሪያት አሳሳል ይህ የአሳሳል አይነት ገፀባሕርያትን ስንገልፅ ገፀባህርያቶቹ ከማህበራዊ ጉዳዬች ጋር ያለቸውን ግኑኝነት፤ የኑሮ ሁኔታ ላይ የተመሰረተ ነው። ይህ የአሳሳል አይነት በአይናችን አይተን መናገርና በቀላሉ መረዳት እንድንችል ያደርገናል። ይህንን ሀሳብ ፈንታሁን እንግዳ በመፅሀፉ እንዲህ አብራርቶታል፦ ከአካላዊ አቋም ገለፃ በማስከተል የሚመጣው የገፀ-ባህሪያ የአሳሳል ደረጃ የሰፋና የጠለቀ ማኀበራዊ ግንኙነትን የሚመለከት ነው፡፡ ይህን የተወሳሰበ ማኀበራዊ ግንኙነት ለማወቅ በመንገደ ስንሄድ ተመልክተን በእርዝመታቸውና በእጥረታቸው ወይም በሽምግልናቸው እና በወጣትነታቸው እንደምንፈርጃቸው ሰዎች (ገፀ ባህሪያት) ልንገነዘባቸው መሞከሩ ከቶ የማይቻል ነገር ነው:: ስለሆነም የእያንዳንዱን ገፀ-ባህሪያት ማኀበራዊ ግንኙነት ለማወቅ የግድ ወደ ተውኔቱ ታሪክ ጠልቆ መግባት ያስፈልጋል:: የትምህርቱን ደረጃ በተመለከተ ለምሳሌ «የተቀረፀው ገፀ-ባህሪ የተማረ ነው ወይንስ ያልተማረ፣ የተማረ ከሆነስ ዘመናዊ ነው ባህላዊ _ ትምህርት የቀሰመው፣ በየት አገርና ከተማስ ተማረ፤ በትምህርቱስ ሰነፍ ነበር ጐበዝ፣» ለሚሉና ለመሳሰሉት ጥያቄዎች መልስ የሚገኝበት ገለፃ እንዲኖር ይፈለጋል። (2009፥28) 8 2.4.3 ስነልቦናዊ የገፀባህሪያት አሳሳል ስነልቦናዊ የገፀባህሪያት አሳሳልአይተን የምንገምተው ወይም የምናውቀው ሳይሆን ውስጣዊ ፍላጎትና ግብ ላይ ትኩረት ያደረገ ነው። ይህንን ሀሳብ ወሰን የለህ ጥላሁን "የፊልም ጥበብ ቅኝት" በሚለው መፅሀፉ እንዲህ ያስረዳል፦ ንቁና ጥንቁቅ በሆኑ ተመልካቾች እንኳን ሊታይና ሊደመጥ የማይችል የውስጣዊ አለም ድርጊት አለ። ገፀባህርይውን በእውነት ለመረዳት ይች አለም አቅፋ የያዘችው የሰው ልጅ ተፈጥሯዊ ሚስጥር አብዛኛውን ጊዜ አስፈላጊ ነው። ወስጣዊ ድርጊት በገፀባህሪያት አእምሮና ስሜት ውስጥ ያለ ሚስጥር፤ ያልተነገሩ ሀሳቦች፤ የቀን ህልሞችን፤ ትውስታዎችን፤ ፍርሀትን፤ ምኞቶችን፤ ቅዤት አጠቃሎ የያዘ ነው። የሰዎችን ባህሪ ለመጨበጥ ተስፋቸውን፤ ህልማቸውን፤ ምኞታቸውን መረዳት አስፈላጊ ነው። በተጨማሪም ፍርሀታቸው አለመረጋጋታቸው ከማንኛውም እውናዊ መቅሰፍት የከፋ ይሆንባቸዋል። (2005፥55) 2.4.4 ግብረ-ገባዊ የገፀባህሪያት አሳሳል ግብረ-ገባዊ የገፀባህሪያት አሳሳል ደረጃ የአንድ ገፀባህሪ የውስጣዊ አመለካከት ማለትም መላካምነቱን ወይም መጥፎነቱን፤ ፅድቁን ወይም ኩነኔውን፤ ቸርነትና ንፉግነቱን፤ ጉረኝነቱንና ትሁትነቱን፤ ድል የማድረግና የመሸነፍ የመሳሰሉትን ሞራላዊ የሆኑ ነግሮችን የምንገልፅበት ነው። ፈንታሁን እንግዳ በመፅሀፉ ስለ ሀሳቡ እንዲህ አብራርቷል፦ ግብረገባዊ የገፀባህሪያት አሳሳል የሚያወሳው እንደ ስነልቦና የገፀባህሪያት አሳሳል ሁሉ በረቂቅ ሀሳቦች ማለትም ህሌናዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ያተኩራል። ልዩነቱ ይሄኛው በሰው ልጅ ፍጥረት የመከባበርና የመዋረድ የሞራል ጥያቄ ላይ መሰረት በማድረግ የሚቀርብ በመሆኑ ነው። ተፈጥሮ ከምትፈቅደው በታች ወርዶ ቅጥ ያጣ ስግብግብነት ሆኖ ሲቀርብ፤ ወይም ከሚገባው በላይ ክብር ፈላጊ ሆኖ ሲቀርብ ወይም ከሁለቱ በተቃራኒ አለማው መንፈዊ መመሪያዎችን እና ህጎችን ተቀብሎ የግብረ ገብ አስተማሪና ሰባኪ መሆንን በሚያሳዩትና በመሳሰሉት ፍሬ ሀሳቦች ላይ በማተኮር ገፀባህሪያትን ከዚህ አንፃር በመቅረፅ ላይ ያነጣጥራል። (2009፥28-29) 2.5 የተዛማጅ ፅሁፍ ቅኝት አጥኝው ከዚህ ጥናታዊ ፅሁፍ ጋር ቀረቤታ ወይም ግኑኝነት ያላቸውን ጥናታዊ ፅሁፎችን በምዕራፍ በመከፋፈል አንድነታቸውንና ልዩነታቸውን ያቀርባል፦ እዮብ ታምሬ 2014 ዓ.ም "የፍቅር ጥግ ፊልም ከገፀባህሪያት አሳሳል አንፃር" በሚል ርዕስ ለወልቄጤ ዩኒቨርስቲ ለቴአትር ጥበባት ት/ት ክፍል ለአርት ባችለር ድግሪ ሟሟያነት ያቀረበው ጥናታዊ ፅሁፍ ነው። በዚህም ጥናታዊ ፅሁፍ ምዕራፍ አንድ መግቢያ፤ የጥናቱ ዳራ፤ የጥናቱ አላማ፤ የጥናቱ አብይ 9 አላማ፤ የጥናቱ ንዑስ አላማ፤ የጥናቱ ጠቀሜታ፤ የጥናቱ ወሰን፤ የጥናቱ ዘዴ፤ በጥናቱ ወቅት ያጋጠሙ ችግሮች፤ ጥናቱ የሚያነሳቸው ጥያቄዎች እንዲሁም የጥናቱ አወቃቀር ተጠቃለው ይገኛሉ። በምዕራፍ ሁለት ክለሳ ድርሳናት፤ የፊልም ምንነት፤ የገፀባህሪያት ምንነት፤ የገፀባህሪያት አሳሳል ደረጃ፤ አካላዊ የገፀባህሪ አሳሳል ደረጃ፤ ማህበራዊ የገፀባህሪ አሳሳል ደረጃ፤ ስነልቦናዊ የገፀባህሪ አሳሳል ደረጃ፤ ሞራላዊ የገፀባህሪ አሳሳል ደረጃ፤ የተዛማጅ ፅሁፍ ቅኝት ይገኛል። በምዕራፍ ሶስት የመረጃ ትንተና፤ የፍቅር ጥግ ፊልም ታሪክ እና የፍቅር ጥግ ፊልም ከገፀባህሪያት አንፃር አሳሳል፤ እንዲሁም በምዕራፍ አራት ማጠቃለያ፤ የመፍትሄ ሀሳብ እና ዋቢ መፅሀፍት ናቸው። ይህ ጥናታዊ ፅሁፍ መሰረት ያደረገው ፊልም ላይ ከመሆኑም ባሻገር በገፀባህሪያት አሳሳል ላይ በመሆኑ አጥኝው ከሚሰራው ጥናታዊ ፅሁፍ ጋር ተመሳሳይነት አለው። ልዩነታቸው ደግሞ ሁለቱም ጥናታዊ ፅሁፎች በተለያዩ ፊልሞች ላይ መሰራታቸው ነው። የምስራች ሞገስ በ2016 ዓ.ም "ባሎችና ሚስቶች ተውኔት ከተውኔት አላባውያን አንፃር ትንተና" በሚል ርዕስ ለወልቂጤ ዩኒቨርስቲ ለቴአትር ጥበባት ት/ት ክፍል ለአርት ባችለር ድግሪ ማሟያነት ያቀረበችው ጥናታዊ ፅሁፍ ነው። ይህ ጥናታዊ ፅሁፍ በምዕራፍ አንድ መግቢያ፤ የጥናቱ ዳራ፤ የጥናቱ አነሳሽ ምክንያት፤ ጥናቱ የሚያነሳቸው ጥያቄዎች፤ የጥናቱ ጠቀሜታ፤ የጥናቱ መጠነ ርዕይ፤ የጥናቱ አላማ፤ የጥናቱ ዘዴ፤ ጥናቱ የሚያነሳቸው ጥያቄዎችና የጥናቱ አወቃቀር ይይዛል። በምዕራፍ ሁለት ክለሳ ድርሳናትና የተዛማጅ ፅሁፍ ቅኝትን ይይዛል። በምዕራፍ ሶስት ጭምቅ ታርክ፤የተዉኔት አላባዉያን ትንተና፤ገፀ ባህር ትንተና፤የባሎች እና ሚስቶች ተዉኔት ወጥ ገፀ ባህር፤የባሎች እና ሚስቶች ተዉኔት አስተኔ ገፀ ባህርይ፤ሴራ፤ቃለ ተዉኔት እና ጭብጥ ያዟል። በምዕራፍ አራት ማጠቃለያና የመፍትሄ ሀሳቦችን እንዲሁም ዋቢ መፅሀፍትን የያዘ ነው። ይህ ጥናታዊ ፅሁፍ መሰረት ያደረገው ተውኔት ላይ ቢሆንም ከአላባውያን አንፃር በመሰራቱ በውስጡም ገፀባህርያትን ስለሚያጠቃልል ከዚህ ጥናታዊ ፅሁፍ ጋር ግኑኝነት እንዲኖረው ያደርገዋል። ልዩነቱ ደግሞ ይህ ጥናታዊ ፅሁፍ መሰረት ያደረገው ተውኔት ላይ በመሆኑ ሁለቱ ጥናታዊ ፅሁፎች የተነሱበት የተለያዩ የኪነጥበብ ዘርፎች ይለያያቸዋል። 10 ምዕራፍ ሶስት 3. የመረጃ ትንተና 3.1 የፀዳል ውስን ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ ታሪክ ታሪኩ የሚያተኩረው ፀዳልና ዳግም በሚባሉ አዲስ ባለትዳሮች ህይወት ላይ ነው። ትዳራቸው አዲስ ሲሆን በአንድ አፖርታማ ውስጥ ተከራይተው ይኖራሉ። ታሪኩም በዋናነት የሚያጠነጥነው ፀዳል በተባለች ሴት ገፀባህርይ የትዳር ህይወት ላይ በሚገጥማት ውስጣዊና ውጫዊ ከራሷ ጋር ከሰዎች ጋር በምታደርገው ግጭት ነው። ፀዳል በህፃንነቷ ወላጆቿ ተለያይተው የአባት ፍቅር ሳታገኝ ያደገች ሴት ናት። በዚህም ምክንያት አባቷ በህልሟ በተደጋጋሚ እየመጣ ትረበሻለች። በዛ ላይ ዳግም ጋር ባላት የትዳር ህይወት ደስተኛነቷን እርግጠኛ አይደለይችም። የዳግም እናት በተደጋጋሚ ወደ ቤታቸው እየመጣች ልጅ እንዲወልዱና ሌሎች ጉዳዮችንም እያነሳች ፀዳል ላይ ተፅእኖ ስታደርግባት ትረበሻለች። ፀዳል አንድ ሶፊ የምትባል የልብ ጓደኛ አለቻት። አንድ ቀን ዳግም ከእናቱ ጋር ገዳም ሲሄድ ፀዳል ሶፊ ጋር ደውላ ለመዝናናት ሀሳብ ታቀርባለች። ሶፊም በሀሳቡ ተስማምታ ማታ ወደ ክለብ ይወጣሉ። ሁለቱም ከመጠን በላይ ስለጠጡ እራሳቸውን ይስቱና ክለብ ውስጥ አንድ ናሆም የተባለ ወጣት አሳዝነውት ቤታቸው ያደርሳቸዋል። በሰዓቱ ሲነቁ ምንም ነገር እንደማያስታውሱ ትነግረዋለች። ሳያወሩም በህይወቷ ደስተኛ እንዳልሆነች ነግራው አመስግናው ይለያያሉ። ዳግም ገዳም ከሄደበት ይመለስና የደበቀችውን የማታውን ነገር ስትነግረው ግጭት ውስጥ ይገባሉ። ከቀናት በኋላም ከሚኖሩበት ቤት ፊትፊት አንድ አዲስ ተከራይ ይገባል። ፀዳል ይህን አዲስ ተከራይ ስታየው ትደነግጣለች። ምክንያቱም ሰክረው ከመጠጥ ቤት ያመጣቸው ናሆም ነበር። ይህ ተከራይና ዳግም በጥሩ ሁኔታ ይግባባሉ። ፀዳልና ናሆም ቀስ በቀስ የተለያዩ ግኑኝነቶችን ይጀምራሉ። ማለትም ዳግም ላይ ያላገኘችውን እንክብካቤና በራሷ ላይ ያላትን አመለካከት የሚቀይር ነገሮችን ከናሆም ታገኛለች። በዚህም መሀል ዳግም ከፀዳል ስልክ የናሆምን ፎቶ አይቶ መጠራጠር ይጀምራል።ዳግም ከእናቱ ጋር ወደ ደብረዘይት ሰው ለመጠየቅ ይሄዳሉ። በዚህ ጊዜ ነበር ፀዳልና ናሆም ነፃነት ያገኙት። ፀዳልም ስላለፈው ህይወቷ ደስተኛ አለመሆኗንና አባቷ ጥሏት እንደሄደ ትነግረዋለች። እሱም አባቷን ለመፈለግ ሀሳብ ያቀርብና ተስማምተው ይለያያሉ። ዳግም እና እናቱ ከሄዱበት ይመለሳሉ። ናሆምና ፀዳል ደብረዘይት አባቷን ለመፈለግ ከዳግም ጋር ተደብቀው ይሄዳሉ። ነገር ግን ፀዳል አባቷን ለማናገር ትፈራና ሳታናግረው ይመለሳሉ። ነገር ግን ፀዳል ቤቷ ስትመለስ ያልጠበቀችው ነገር ይፈጠራል። ዳግም ናሆም የሆነ ጊዜ የሰጣትን ሸሚዝ አግኝቶ የሁለቱን ግንኙነት ደርሶበት ይጠብቃቸዋል። በዚህም ሶስቱ ትልቅ ችግር ውስጥ ይገባሉ። ዳግም በጣም ትልቅ ምሬት ውስጥ ስለገባ ናሆም ላይ ይሰነዝራል።በዚህም ፀዳል ከዳግም ጋር ትጣላለች። አልጋቤት ተከራይታ ከቤት ትወጣናከናሆም ጋር አብረው ሆነው እንደምትወደው ትነግረዋለች። ሶፊ ደውላ ተገናኝተው ስለተፈጠረው ነገር ስትነግራት አለመግባባት ይፈጠርና ይጣላሉ። ከዛም ፀዳል በንዴት ወደ ናሆም ቤት ስትሄድ የከራየውን 11 ቤት ለቆ ሄዶ ነበር። ለፀዳልም አንድ መልዕክት ቢያስቀምጥም መልዕክቱ ላይ ግን የት እንደሄደ አልፃፈም። ፀዳልም በዚህ ግራ በሚያጋባ ሁኔታ ወዴት መሄድ እንዳለባት ይጠፋትና ጭንቀት ውስጥ ትገባለች። ከዛም ወደ ዳግም ቤት በመሄድ ይቅርታ ትጠይቅና ይቅር ይላታል። ከሶፊም ጋር ይታረቃሉ። ኑሯቸውን ይጀምሩ እና እየኖሩ እያለ የዳግም አናት እና ሶፊ ቡና ለመጠጣት ቤታቸው ይመጣሉ። በዚህ መሀል ሰራተኛ ቀጥረው ነበር። የዳግም እናት ግን ፀዳልን በነገር ስትነካት የድሮ ቁስል ይነሳባትና ቁስሏ እንዳልዳነ ትረዳዋለች። ከዛም አባቷን ፈልጋ የማግኘት ውሳኔ ላይ ደረሰችና ዳግምን ይቅርታ ትጠይቅና እራሷን አክማ መመለስ እንዳለባት ትነግረውና ቀጥታ አባቷን ፍለጋ ደብረዘይት ትሄድና ሁሌም በህልሟ እየመጣ የሚያስጨንቃትን አባቷን ታገኘዋለች። 3.2 የፀዳል ውስን ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ ገፀባሕርያት አሳሳል 3.2.1 ፀዳል ሀ. የፀዳል አካላዊ አሳሳል ፀዳል በዚህ ፊልም ላይ ዋና ገፀባህርይ ስትሆን የፊልሙ ታሪክ በእሷ ላይ የተመሰረተ ነው። በክፍል 7 ደቂቃ 8:51 እስከ 9:21 እንዲሁም ደቂቃ 18:21 እስከ 19:21 ደቂቃ ላይ ባለው ደቂቃ ውስጥ ፀዳል እድሜዋ 27 እንደሆነ መረዳት ይቻላል። በዚህም ጊዜ ፀዳል አባቷ ጥሏት የሄደው በሰባት አመቷ እንደሆነ እና አባቷን ለመፈለግ ከ20 አመታት በኋላ ከናሆም ጋር ፍለጋ እንደወጡ በቃለ ተውኔታቸው ይናገራሉ። ፀዳል አብዛኛውን ጊዜ ረዘም ያለ ቀሚስ የምትለብስ፤ ረዘም ያለች፤ ረዥም ፀጉር ያላት ገፀባህርይ ናት። ለዚህም የፀዳል የሰውነት አቋም በቀላሉ የገፀባህሪዋን አካላዊ ማንነት፤ ያችበትን ስሜት፤ የህይወት ደረጃ መመልከት ይቻላል። ለ. የፀዳል ማህበራዊ አሳሳል በክፍል ሰባት ደቂቃ 3:18 አስከ 7:50 ባለው ደቂቃ ውስጥ በፊልሙ ታሪክ ፀዳል ለቤተሰቧ አንድ ልጅ ስትሆን አባቷ እና እናቷ በልጀነቷ ተለያይተው በእናት ብያ ያደገች እንዲሁም የትምህርት ደረጃዋ ከዩኒቨርስቲ የተመረቀች ናት። ቤተሰቦቿ ከመለያየታቸው በፊት አባቷን በጣም የምትወድ ገፀባህርይ ናት። ምክንያቱም በክፍል ሁለት ደቂቃ 2:30 ላይ ፀዳል ከአባቷ ጋር እየተሳሳቀች ምግብ ስትበላ እናያለን። በተጨማሪም በክፍል 7 ደቂቃ 4:34 እስከ 7:38 ባለው ቆይታ ፀዳል ከአባቷ ጋር ጥሩ ግኑኝነት እንደነበራትና እንደምትወደው ትናገራለች። በክፍል 1 ደቂቃ 23:30 እሰከ 31:55 ባለው ቆይታ ፀዳል ከጓደኛዋ ሶፊ ጋር እየተዝናናች እና እየተሳሳቁ ሲጫወቱ እናያለን። በተጨማሪም የፀዳል የልብ ጓደኛ ሶፊ እንደሆነች በክፍል አንድ ደቂቃ 21:09 እስከ 22:09 ባለው ቆይታ ፀዳል ከሶፊ ጋር በስልክ መልዕክት ስትፃፃፍ እና ሲያወሩ እናያለን። በዚህም ሁለቱ ጥሩ የሆነ ግኑኝነት እንዳላቸው ያሳያል። በሌላ በኩል ደግሞ ፀዳል አዲስ ወደ ህይወቷ ለሚመጣ ሰው ልቧ ክፍት እንደሆነ እና የልቧን ሀሳብ እንደምታካፍል በክፍል 2 ደቂቃ 12:00 እስከ 13:03 ድረስ ፀዳል ከናሆም ጋር በምታደርገው ቃለ ተውኔት እናያለን። በተጨማሪም በክፍል 5 12 ደቂቃ 12:42 እስከ 16:05 ባለው ፀዳል ከስራ ባልደረባዎቿ ጋር ስትቀላለድ እና ስለ ስራ ጉዳዬች ሲያወሩ ይታያሉ። ይሄ ደግም ከስራ ባልደረባዎቻ እና በዙሪያዋ ካሉት ሰዎች ጋር ጥሩ የሚባል ግኑኝነት እንዳላት ያሳያል። ሐ.የፀዳል ስነ-ልቦናዊ አሳሳል ፀዳል በፊልሙ ሁሉም ክፍሎች በህልሟ የምታየው አባቷ ተፅዕኖ ይታያል። በክፍል 1 ከደቂቃ 9:50- 10:48 ባለው ውስጥ ፀዳልን የዳግም እናት ስታዛትና የቤት ስራዎችን እሷ እንድትሰራ ተፅዕኖ ስታደርግ ይታያል። ፀዳልም በጋብቻ ህይወቷ ደስተኛ አይደለችም። በፊልሙ የመጀመሪያ ክፍል ጀምሮ መቀዝቀዝ ያለ ድባብ ይታያል ስትስቅም አትታይም። በክፍል 1 ደቂቃ 25:45 ላይ ከልብ ጓደኛዋ ጋር ስትስቅ እና ስትደሰት ትታያለች። ስለዚህ ፀዳል በትዳራ ደስተኛ አይደለችም ማለት ነው። በክፍል 6 ደቂቃ 14:10 ፀዳል በምርቃቷ ቀን ማግባቷን ትናገራለች ስለዚህ ተሎ ያገባችበት ምክንያት ወይም ዳግምን ሳታስበው ማግባቷ የአባቷን ፍቅር አጥታ ማደጓ ያመጣባት ተፅዕኖ ነው። እንዲሁም በክፍል 5 ደቂቃ 25:8 ላይ ናሆም ትወጅዋለሽ ብሎ ሲጠይቃት ባሏን መስሏት ደንግጣ ማንን ትላለች። ስለዚህ እርጥጠኛ ያልሆነችበት የፍቅር እና የትዳር ህይወት እየኖረች እንደሆነ ያሳያል። ሌላኛው በክፍል 4 ደቂቃ 20:29 በእልሟ ህፃን እያለች እናቷ የምታደርስባትን ተፅዕኖ ስታስታውስ እና የድሮ ፎቶዎችን እያየች ስታለቅስ ይታያል ይሄም በፀዳል ስነልቦና ላይ ተፅዕኖ ሲያደርስባት እናያለን። በክፍል 6 ደቂቃ 15:00 ላይ ናሆም ፀዳልን ደስተኛ እንደሆነች ሲጠይቃት እንጃ ብላ ደስተኛነቷን ትጠራጠራለች። ነገር ግን ዳግም እሷን ደስተኛ ለማድረግ ቢጥርም እሷ ግን ደስተኛ መሆን አልቻለችም። ይልቁንም ናሆም ስለሚሰማት፤ ስለሚረዳት፤ ለሷ በመጨነቅ ስለሚጠይቃት ደስተኛ እንዲያደርጋት ትናገራለች። በዚህም ምክንያት ከአባቷና ከዳግም ያጣችውን ነገር ናሆም ላይ ስላገኘች ዳግም ላይ ልትማግጥ ችላለች። ካለአባት የሚያድጉ ልጆች ይበልጥም ሴት ልጅች ካደጉ በኋላ በህይወታቸው ምን አይነት ማንነት እንደሚኖራቸው በፀዳል ገፀባህርይ ማየት ይቻላል። በተጨማሪም በክፍል 7 ደቂቃ 2:52-4:00 ድረስ ፀዳል አባቷን በጣም እንደምትወደውና በልጅነቷ እንዳጣችው እንዲሁም በዛ ተፅዕኖ የተነሳ ብቻውን የቆመች ያህል እንደሚሰማት ታወራለች። ይሄም በህፃንነቷ ባጣችው ነገር በራስ አለመተማመን እና የጎደለ ነገር እንዳላት እንደሚሰማት እንዲሁም ያንን ለመሙላት ከሌላ ሰው ጋር ሌላ ግንኙነት እንድትጀምር ሲያደርጋት ይታያል። ሐ. የፀዳል ግብረ-ገባዊ አሳሳል በክፍል 2 ደቂቃ 11:46-11:50 ድረስ ፀዳል ከናሆም ጋር እያወራች አፏን ትይዛለች። ያኔም በራስ አለመተማመኗንና ለራሷ ጥሩ አመለካከት እንደሌላት ያሳያል። ሌላኛው በክፍል 2 ደቂቃ 12:18-15:35 ድረስ ፀዳል ሁሉም ነገር ስልችት እንዳላት መተንፈስ እስኪያቅታት ድረስ እንደምትጨነቅ እንዲሁም መኖር የሌለባትን ህይወት እይኖረች እንደሆነ ትናገራለች። ይሄም የዳግምና የእሷ የስነምግባር ልዩነት እና የአስተዳደግ ልዩነት የተነሳ ነው። በክፍል 2 ደቂቃ 31:55 ናሆም ለሊት ስለቁንጅናዋ የነገራትን እያስታወሰች እራሷን ፊት ለፊት በመስታውት ስታይ እራሷን በተለየ ምልከታ ታስተውለዋለች። በዚህም 13 የስነምግባር ለውጥ እናያለን። በክፍል 6 ደቂቃ 20:10 ላይ ፀዳል ከናሆም ቤት ሆና የዳግም እናት ስትመጣባት ትሸውዳትና ቤት ስትገባና ስትዋሽ እናያለን። ፀዳል በህፃንነቷ የተፈጠረባት ተፅዕኖ በትዳሯ ላይ ፀንታ እንዳትኖር እና ቋሚ የሆነ ማንነት እንዳይኖራት አድርጓታል። 3.2.2 ዳግም ሀ. የዳግም አካላዊ አሳሳል በክፍል 6 ደቂቃ 13:50- 14:00 ባለው ጊዜ የዳግም እድሜው 25-30 የሚገኝ ነው። በክፍል6 ደቂቃ 13:57-14:25 ድረስ ባለው ዳግም ረዘም ያለ ሰውነት ያለው አብዛኛውን ጊዜ ከላይ ሸሚዝ እና ጃኬት እንዲሁም ከታች ጅንስ ሱሪ የሚያረግ ወጣት ገፀባህርይ ነው። ለ. የዳግም ማህበራዊ አሳሳል ዳግም አንድ በእናቱ ብቻ ያደገና ከእናቱ ጋር የጠበቀ ግኑኝነት አለው። ዳግም የፀዳል ባል ሲሆን በክፍል 3 ደቂቃ 18:30-19:38 ድረስ ናሆም ከቤታቸው ፊትለፊት ተከራይቶ ሲገባና ጥሩ ጎረቤት እንደሚሆኑ ሲነግረው ዳግም ለሰዎች ያለው አመለካከት ጥሩ እንደሚባል ያሳያል። ሌላኛው ደግሞ በክፍል 2 ደቂቃ 33:18-35:04 ድረስ የዳግም ጓደኞች ቤቱ መጥተው ምግብ ሲበሉ ይታያሉ። በዚህም ደግሞ ከጓደኞቹም ጋር ጥሩ ግኑኝነት እንዳለው ያሳያል።በተጨማሪም በክፍል 9 ደቂቃ 10:45-13:00 ድረስ ባለው ዳግም ናሆምን ቀጥሮ ፀዳልን እንደሚወዳትና እንዲተውለት ሲጠይቀው እናያለን ይህም ደግሞ ሚስቱን ከልቡ እንደሚወዳትና ከሚስቱ ጋር ቀሪ ህይወቱን ማሳለፍ እንደሚፈልግ ያሳያል። ዳግም ከእናቱ ጋር የጠበቀ ግኑኝነት ያለውና በእናቱ ብቻ ያደገ ገፀባህርይ ነው። በክፍል 2 ደቂቃ 14:18 ላይ ዳግም ከእናቱ ጋር ገዳም ሲሄድ ይታያል። ዳግም ከእናቱ ጋር የጠበቀ ግኑኝነት ከመኖሩ የተነሳ እናቱ በትዳር ሂወቱ ጣልቃ ሲትገባ ብዙም ምላሽ አይሰጥም። በስራውም በአንድ መስሪያ ቤት ተቀጥሮ ይሰራል። በእነዚህ ምክንያቶች ዳግም ጥሩ የሚባል ማህበራዊ ግኑኝነት አለው ማለት ይቻላል። ሐ. የዳግም ስነልቦናዊ አሳሳል በክፍል 3 ደቂቃ 20:46-22:54 ባለው ፀዳል የቤት ሰራተኛ መቅጠር እንዳለባቸው ስትነግረው ዳግም ገቢ ለመቆጠብና ያለ አግባብ ብር ማውጣት እንደሌለባቸው ገልፆ የቤቱን ስራ እንደሚያግዛት ይነግራታል። በቀልድም መልክ የሰራተኛዋን ክፍያ ለእኔ ክፈይኝና እኔ እሰራለሁ ሲል ይመልሳል። ደግሞ እራሱን ዝቅ አድርጎ የሰራተኛ ስራ ለመስራት መዘጋጀቱ የእሱን የስነልቦና ጥንካሬ ያሳያል ምክንያቱም ወደፊት ከሚስቱ ጋር እና ከወላጁ ጋር ለመኖር የሚያስበውን ቤቱን ለመስራት ሲል ነው። ነገር ግን የቤት ሰራተኛዎች የሚሰሩትን ስራዎችን በፊልሙ ሲሰራ አይታይም። ይህ ደግሞ ፊልሙን ለሚመለከተው ሰው ጥሩ ስነልቦና እንዳለው ማሳየት አልተቻለም። ነገር ግን ህይወቱን ለመቀየር እና ለመለወጥ ከሚያደርገው ጥረት አንፃር ጥሩ የሚባል ስነልቦናዊ አሳሳል ይታይበታል። 14 መ. ግብረ-ገባዊ አሳሳል በክፍል 1 ደቂቃ 15:39 ላይ ስንመለከት ዳግም በሚስቱ የሚከበር፤ ትሁትና ጥሩ ግብረገብ ያለው ነበር። በክፍል 3 ደቂቃ 3:57-5:45 ባለው ስንመለከት ደግሞ ፀዳልን ሲሰድባትና ሲያስቀይማት የሚያጋጥመውን የግብረገብ ለውጥ እናያለን። ምክንያቱም በክፍል1 ደቂቃ 27:28 ላይ ዳግም ወደ ገዳም ሲሄድ ፀዳልና ሶፊ መጠጥ ቤት ሂደው ስለነበረ ነው። እንዲሁም በክፍል 5 ደቂቃ 2:29-7:55 ድረስ ባለው ዳግም ጭፈራ ቤት ናሆምን ሲያየው የቅናትና የጥላቻ ስሜት ይታይበታል። እናም ፀዳልን እንደንስ ብሎ ሲያስጨንቃት እናያለን። ምክንያቱም በክፍል 4 ደቂቃ 27:28-27:50 ባለው ዳግም የናሆምን ፎቶ ከፀዳል ስልክ ስላገኘ እና ስለጠረጠራቸው ነው። 3.2.3 ናሆም ሀ. የናሆም አካላዊ አሳሳል በክፍል 9 ደቂቃ 27:41 ሶፊ የናሆም እድሜው ሀያ እንደማይሞላና ፀዳል ከሱ ጋር መሆኗ ልክ አለመሆኑን ትገልፅላታለች። ስለዚህ ናሆም እድሜው ከ18-20 ውስጥ የሚገኝ ነው። ናሆም መካከለኛ ቁመት ያለው፤ ፀጉሩን የሚያሳድግ፤ ጥሩ አቋም ያለው፤ መልከመልካም፤ ሲናገር የተረጋጋ እና ስራ ሲኖረው ሸሚዝ በጅንስ ሱሪ ወይም ቤት ሲሆን ቲሸርት በቱታ ሱሪ አብዛኛውን ጊዜ የሚለብስ ወጣት ገፀባህርይ ነው። እንዲሁም በክፍል 4 ደቂቃ 16:19 ላይ የዳግም እናት መልከመልካም አንደሆነ ትገልፃለች። ለ. የናሆም ማህበራዊ አሳሳል በክፍል 5 ደቂቃ 25:55 ላይ ናሆም ቤተሰቦቹ ውጭ ሀገር እንደሚኖሩና እሱ ብቻውን እዚህ ሀገር እንደሚኖር ይናገራል። ሌላኛው በክፍል 3 ደቂቃ 19:43 ላይ ተከራይቶ ሲገባ ዳግም ሲያግዘውና ጥሩ ጎረቤት እንደሚሆኑ ሲነግረው እሱም ቤቱን ካስተካከለ በኋላ ቤቱ እንደሚጋብዘው ይነግረዋል። ነገር ግን በክፍል 7 ደቂቃ 18:03 ላይ ዳግም ናሆምን በቦክስ ሲመታው እናያለን። ምክንያቱም ናሆም ከዳግም ሚስት ጋር ፍቅር ውስጥ ስለገባ ነው። በዚህም የናሆም ማህበራዊ አሳሳል ሲቀያዬር እንመለከታለን። ይህም እንዲፈጠር ያደረገው ናሆም ብቻውን መኖሩና ቤተሰቦቹ ውጭ ሀገር መሄዳቸው በናሆም ማህበራዊ ህይወቱ ላይ ተፅዕኖ ሲያደርስበትና ከባለትዳር ሴት ጋር እንዲሆን ሲጋብዘው እንመለከታለን። ሐ. የናሆም ስነልቦናዊ አሳሳል በክፍል 5 ደቂቃ 26:00-26:48 ድረስ ባለው ፀዳል ናሆምን ለምን ብቻውን እንደሚኖር ስትጠይቀው እሱ እየለፋ መኖር የማይፈልግ ሰው መሆኑን፤ ሁሌም የሚሞት ሰው እንደሆነ በማሰብ አንደሚኖር እንዲሁም ለገንዘብ ግድ የሌለው ሰው መሆኑንና ፍላጎቱን የሚንርሰው መሆኑን ይናገራል። በደቂቃ 24:43-24:54 ባለው ደቂቃ ጠዋት ወጥቶ ማታ የሚገባበትን ስራ ደባሪ ስራ ብሎ ሲጠራው ይሰማል። ለዚህም ዲጄ፤ ቪድዮ 15 ኤዲቲንግ፤ ግራፊክስ ዲዛይን እየሰራ እንደሚኖር ይናገራል። ስለዚህ ናሆም በስነልቦና አሳሳሉ ደካማ ነው ማለት ይቻላል። መ. የናሆም ግብረ-ገባዊ አሳሳል ናሆም በዙሪያው ላሉ ሰዎች አሳቢ እና መልካም ግብረ ገብ ያለው ወጣት ነው። በክፍል 1 ደቂቃ 30:35-ክፍል 2 ደቂቃ 21:47 ድረስ ፀዳልና ጓደኛዋ ሶፊ መጠጥ ቤት ሰክረው እራሳቸውን መቆጣጠር ሲያቅታቸው ናሆም እነሱን ሲያግዛቸው እንዲሁም ቤታቸው ድረስ አምጥቶ ሽሮ ፈትፍቶ ሲሰራላቸው ይታያል። እንዲሁም በክፍል 4 ደቂቃ 14:02-15:00 ድረስ ናሆም የዳግም እናት ፀበል በጀሪካን ይዛ ሲያግዛት እንመለከታለን። በዚህም በዙሪያ ለሚገኙት ሰዎች መልካም ተግባሩን ሲያደርግ እንመለከታለን። ናሆም በእነዚህ ምክንያቶች ጥሩ የሚባል ግብረገብ እንዳለው መረዳት ይቻላል። 3.2.4 የዳግም እናት ሀ. የዳግም እናት አካላዊ አሳሳል የዳግም እናት አካላዊ ማንነቷ ፊልሙ ተጀምሮ እስኪያልቅ ድረስ የማይለወጥ ነው። አካላዊ ማንነቷ መጠነኛ ቁመት ያላት፤ እድሜዋ በአምሳዎቹ ውስጥ የሚገመት፤ በአለባበሷ ደግሞ ብዙ ጊዜ ልብሶችን ደራርባ የምትለብስ ገፀባህርይ ናት። በፀዳል ውስን ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ ላይ የዳግም እናት አካላዊ ማንነቷ የተገለፀበት በክፍል 1 ደቂቃ 10:29 ላይ ሲሆን እናቱ ወደ ዳግም ቤት ጓዟንን ይዛ ስትመጣ በዛን ወቅት ቀሚስ፤ ነጠላና ከላይ ፎጣ የለበሰች ሲሆን በተጨማሪም በክፍል 3 ደቂቃ 15:11 ላይ እራሱን አለባበስ ለብሳ ትታያለች። በዚህም ገፀባህርይዋ የለበሰችው አለባበስ የጊዜ ለውጥ አላሳየም። ለ. የዳግም እናት ማህበራዊ አሳሳል የዳግም እናት አንድ ዳግምን ብቻ የወለደችና ከባሏ ጋር ተለያይታ የምትኖር ገፀባህርይ ናት። እንዲሁም ትርሲት የምትባል የአደራ ልጅ ደብረዘይት ያላት ሲሆን በክፍል 6 ደቂቃ 25:33 ላይ የአደራ ልጇ ልትወልድ ሆስፒታል ስትገባ ልትጠይቃት ዳግምን ይዛ ስትሄድ እናያለን። በዚህም የዳግም እናት ከሰዎች ጋር ጥሩ ግኑኝነት እንዳላት እና በሰዎች ዘንድ አደራ እስከመስጠት ድረስ እንደምትታመን ያሳያል። የዳግም እናት ቤተክርስቲያን እና ገዳም አብዝታ የምትመላለስ በመንፈሳዊ ህይወቷ ጠንካራ የምትባል ገፀባህርይ ስትሆን ከዳግም ጋር የቀረበ ግኑኝነት ያላት እና በሱ ጉዳይ ላይ ጣልቃ የምትገባ ገፀባህርይ ናት። ሐ. የዳግም እናት ስነልቦናዊ አሳሳል የዳግም እናት ስነልቦናዊ አሳሳሏን ስንመለከት በዳግም ህይወት ወይም በትዳሩ ላይ ጣልቃ የምትገባ እሷ የምትሰጠው አስተያየት አስፈላጊ ነው ብላ የምታስብ ገፀባህርይ ናት በክፍ 3 ደቂቃ 13:55 ላይ ስንመለከት ዳግምን ቁርስ ፓንኬክ እንዳይበላ ስትነግረው እንመለከታለን እንዲሁም በክፍል 10 ደቂቃ 18:18 ላይ የቤት 16 ሰራተኛዋ ቡናውን እንድትቆላው ስታዛት እንመለከታለን። በዚህም ፀዳል ዳግምን ጥላው እንድትሄድ ስታደርጋት እናያለን። የዳግም እናት የእነሱን ስሜት የማታከብርና የራሷን ስሜት ብቻ የምትናገር እናም ልክ ነኝ ብላ የምታስብ ገፀባህርይ ናት። መ. የዳግም እናት ግብረገባዊ አሳሳል የዳግም እናት በክፍል 3 ደቂቃ 14:37 ላይ ስንመለከት ዳግም እሷ የምትፈልገውን የማድረግ ግዴታ እንዳለበት ሲነግራት እሷ የምትፈልገው ልጅ ትነግረዋለች። በዚህ ጉዳይ ከአንድም ሁለቴ እንዲወልዱ ስትነዘንዛቸውና በዚህም ምክንያት ዳግምና ፀዳል ሲያዝኑ እናያለን። በተጨማሪም የቤት ስራዎችን ፀዳል እንድትሰራ የምትፈልግ ሲሆን በዚህም ሳይታወቃት ፀዳል ላይ ተፅዕኖ ስታደርስ ይታያል። በክፍል 1 ደቂቃ 9:40 ላይ ፀዳል ሻይ በማንቆርቆሪያ ሰታመጣ እና ዳግም ሻዩን በፌርሙዝ ሲቀይረው የዳግም እናት ፀዳልን አሷ መገልበጥ እንዳለባት። ስትወቅሳት እናያለን። 3.2.5 ሶፊ ሀ. የሶፊ አካላዊ አሳሳል ሶፊ መካከለኛ ቁመት ያላት፤ የሰውነት አቋሟ ወፈር ያለች፤ አድሜዋ ከ25-30 የሚገመት ሲሆን አለበባሷ ቀሚስና ሱሪ በቲሸርት የምትለብስ ገፀባህርይ ናት። በፀዳል ውስን ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ ላይ ሶፊ አካላዊ ማንነቷ በመጀመሪያ ጊዜ የታየው በክፍል 1 ደቂቃ 23-26 ላይ ሲሆን በዚህም ጊዜ ቀሚስ ለብሳ ነበር። ለ. የሶፊ ማህበራዊ አሳሳል ማህበራዊ አሳሳሏን ስንመለከት ሶፊ የፀዳል የቅርብ ጓደኛዋ ስትሆን በክፍል1 ደቂቃ 27:37-31:05 ድረስ ሶፊና ፀዳል አብረው ሆቴል ገብተው ሲዝናኑ እናያለን በዚህም ሶፊ ከጓደኛዋ ጋራ ባላት ግኑኝነት ጥሩ የሚባል ማህበራዊ አሳሳል እንዳላት መረዳት እንችላለን። በተጨማሪም ሶፊ ከፀዳል ባል ከዳግም ጋር እና ከዳግም እናት ጋር በምታደርገው ቃለተውኔት በዙሪያዋ ካሉት ሰዎች ጋር ጥሩ ግንኙነት እንዳላት ያሳያል። ሐ. የሶፊ ስነልቦናዊ አሳሳል ሶፊ ስነልቦናዊ አሳሳሏን በክፍል 9 ደቂቃ 26:28-28:39 ድረስ ስንመለከት ፀዳል ከዳግም ጋር ተጣልታ ከወጣች በኋላ ሶፊን ስታገኛት ፀዳል ያደረገችው ነገር ልክ እንዳልሆነና ወደ ትዳሯ እንድትመለስ ስትነግራትና ልታስታርቃቸው ስትጥር እናያለን በዚህም ሶፊ የትዳርን ክቡርነት የምታምን ገፀባህርይ እንደሆነች ማወቅ ይቻላል። 17 መ. የሶፊ ግብረገባዊ አሳሳል የሶፊን ግብረገባዊ አሳሳል በክፍል ሶስት ደቂቃ 15:36-16:29 ድረስ ባለው ስንመለከት ፀዳል ዳግምን ለመዝናናት ወደ ሎጅ እንሂድ ስትለው እና ዳግም ሀሳቡን ሲያስጨነግፍ እናያለን። በዛው ሰአትም ሶፊ መሄድ እፈልጋለው ብላ ነበር። ነገር ግን የዳግምን መልስ ስትመለከት ሀሳበዋን ትቀይርና እየቀለዱ መሆናቸውን ትነግረዋለች። በተጨማርም በክፊል 9 ደቅቃ 26-28 እስከ 28:39 ባለዉ ክፊል ሶፊ ዳግም እና ፀዳልን ልታስ ታርቅ ስትጥር እናያለን በዝህም ሶፊ የጓደኛዋ ህይወት እንድበላሽ የማትፈልግ እና ሁለቱ በትራቸዉ ፀንተዉ እንድኖሩ የምትፈልግ ገፀ-ባህር ናት። 18 ምዕራፍ አራት 4 ማጠቃለያ ይህ ጥናታዊ ጽሁፍ ፀዳል ዉስን ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ ከገፀ ባህርያት አንፃር በመተንተን የምዳስስ ስሆን በፊልሙ ያሉትን ነፀ ባህርያት የተሳሉበትን መንገድ በአራቱም የገፀ ባህርያት አሳሳል አንፃር በመተንተን ያስቀምጣል። በዝህ መሰረት ፀዳል በፊልሙ ላይ እንደት በገፀ ባህር አንፃር እንደተሳለች ፊልሙን በመመልከት አካላዊ ማንነቷ ምን እንደምመስል ፣ማህበራዊ ሁነታዋ እንደት እንደተሳለች ፣በስነ- ልቦና በኩል በምን መልኩ እንደተገነባች እና ግብረ ገባዊነቷን እንደት እንደተሳለች በማየት በመተንተን ያስቀምጣል። በተመሳሳይ የዳግም ገፀ-ባህር አካላዊ ማንነቱ ምን አይነት እንደሆነ ፣ማህበራዊ ሁነታዉ ምን እንደሆነ በስነ-ልቦና እንደት እንደተሳለ እና ግብረ-ገባዊ ማንነቱ ምን አይነት ሰዉ እንደሆነ ተተንትኖበታል ።እንድሁም ናሆም በአካላዊ ነጽታ ምን አይነት እንደሆነ ፣ማህበራዊ ሁነታዉ ምን አይነት እንደሆነ ፣በስነ-ልቦናዊ በኩል እንደት እንደተሳለ በተጨማርም ግብረ-ገብዊ ማንነቱ ምን አይነት እንደሆነ ያስቀመምጣል። እንድሁም የዳግም እናት ገፀ-ባህር በአካላዊ ማንነቷ ምን አይነት እንደሆነች ምህበራዊ ሁነታዋ ምን አይነት ሴት እንደሆነች ፣በስነ ልቦናዊ ማንነቷ እና በግብረ-ገባዊ ማንነቷ እንደት እንደተገነባች ያስቀምጣል። ሌላኛዋ ገፀ-ባህር ሶፊ በአካላዊ ማንነቷ ፣ በማህበራዊ ሁነታዋ ፣ በስነ-ልቦናዊ ማንነቷ እና በግብረ-ገባዊ ማንነቷ በገፀ-ባህር አሳሳል እንደት እንደተሳለች ተተንትናለች። በዝህ መሰረት ደራሲው ግልጽ እና ታአማኒነት ያላቸዉን ገፀ-ባህር በፊልሙ ላይ ተጠቅሟል።በተጨማርም አብዛኛዎችን ገፀ-ባህርያት በአራት ገፀ-ባህር አሳሳል ደረጃ በጥሩ እና አሳማኝ በሆነ መልኩ እንደሳላቸዉ ተመልክተናል። 19 4.1 የመፊትሄ ሀሳብ አጥኝዉ ይህን ጥናታዊ ጽሁፍ ፀዳል ዉስን ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ ከገፀ-ባህርያት አሳሳል አንፃር ትንተናን በምን መልኩ ተሰርቷል የምለዉን ስመለከት ጥቂት ስህተት መመልከት ችሏል በመሆኑም ይሄን ክፍተት ልቀርፊ ይችላል በማለት እንደመፍትሄ ሃሳብ ያነሳዉን ሀሳብ እንደምከተለዉ ያቀርባል ። ፨ የዳግም እናት የለበሰችዉ ልብስ በክፊል ልዩነት ዉስጥ ተመሳሳይ ስሆን ይሄም የግዜ ለዉጥን አላሳየም ይሄንን የግዜ ለዉጥ ለማሳየት በክፊል ልዩነት ዉስጥ የተለያየ ልብስ መልበስ ይኖርባታል። 20 ዋቢ መጽሀፋት አድስ ተስፋ(2005)።የፊልም ድርሰት አፃፃፊ ብልሃት።አድስ አበባ።ዚአድ ማተሚያ ቤት። ዘላለም ተፈራ(2010)።የፊልም ትወና ጥበብ። አድስ አበባ።ፋር ኢስት ትሬድንግ ማተሚያ ቤት። ወሰን የለህ ጥላሁን(2005)።የፊልም ጥበብ ቅኝት።አድስ አበባ።ፋር ኢስት ትሬድንግ ማተሚያ ቤት። ፋንታሁን አንግዳ(2009)።የተዉነት ድርሰት አፆፆፊ ዘዴ።አድስ አበባ። konstantin stanislavski(1949)።building a character።usa።theatre arts books። Lajos egri(1946)።the art of dramatic writing።new york።simon and schuster። ምስጋና አበርክቶ አጠቃሎ ምዕራፍ አንድ 1. መግቢያ 1.1 የጥናቱ ዳራ 1.2 የጥናቱ አላማ 1.2.1 የጥናቱ አብይ አላማ 1.2.2 የጥናቱ ውስን አላማ 1.3 የጥናቱ ጠቀሜታ 1.4 ጥናቱ የሚያነሳቸው ጥያቄዎች 1.5 የጥናቱ ዘዴ 1.6 የጥናቱ ወሰን 1.7 የጥናቱ አደረጃጀት ምዕራፍ ሁለት 2.ክለሳ ድርሳናት 2.1 የፊልም ምንነት 2.2 የፊልም ፅሁፍ አላባውያን 2.3 የገፀባህሪያት ምንነት 2.4.ገፀባሕርያት የሚሳሉበት መንገዶች 2.4.1 አካላዊ የገፀባህሪያት አሳሳል 2.4.2 ማህበራዊ የገፀባህሪያት አሳሳል 2.4.3 ስነልቦናዊ የገፀባህሪያት አሳሳል 2.4.4 ግብረ-ገባዊ የገፀባህሪያት አሳሳል 2.5 የተዛማጅ ፅሁፍ ቅኝት ምዕራፍ ሶስት 3. የመረጃ ትንተና 3.1 የፀዳል ውስን ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ ታሪክ 3.2 የፀዳል ውስን ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ ገፀባሕርያት አሳሳል 3.2.1 ፀዳል ሀ. የፀዳል አካላዊ አሳሳል ለ. የፀዳል ማህበራዊ አሳሳል ሐ.የፀዳል ስነ-ልቦናዊ አሳሳል ሐ. የፀዳል ግብረ-ገባዊ አሳሳል 3.2.2 ዳግም ሀ. የዳግም አካላዊ አሳሳል ለ. የዳግም ማህበራዊ አሳሳል ሐ. የዳግም ስነልቦናዊ አሳሳል መ. ግብረ-ገባዊ አሳሳል 3.2.3 ናሆም ሀ. የናሆም አካላዊ አሳሳል ለ. የናሆም ማህበራዊ አሳሳል ሐ. የናሆም ስነልቦናዊ አሳሳል መ. የናሆም ግብረ-ገባዊ አሳሳል 3.2.4 የዳግም እናት ሀ. የዳግም እናት አካላዊ አሳሳል ለ. የዳግም እናት ማህበራዊ አሳሳል ሐ. የዳግም እናት ስነልቦናዊ አሳሳል መ. የዳግም እናት ግብረገባዊ አሳሳል 3.2.5 ሶፊ ሀ. የሶፊ አካላዊ አሳሳል ለ. የሶፊ ማህበራዊ አሳሳል ሐ. የሶፊ ስነልቦናዊ አሳሳል መ. የሶፊ ግብረገባዊ አሳሳል ምዕራፍ አራት 4 ማጠቃለያ 4.1 የመፊትሄ ሀሳብ ዋቢ መጽሀፋት